በፈረንሳይ ቅጥነት ውበት ነው፥፥ ከልክ ያለፈ መገርጣት ግን አሁን በህግ ያስቀጣል::
ፈረንሳይ ከልክ በላይ የሚከሱ የፋሽን ሞዴሎችን አና ሞዴሎችን ከልክ ላለፈ ቅጥነት የሚዳርጉ ድርጅቶችን ልታግድ ነው::
የፈረንሳይ መንግስት በቅርቡ የሚያፀድቀው ህግ የፋሽን ሞዴሎች ከልክ በላይ እንዲከሱ የሚያደርጉ ድርጅቶች ላይ የ ሰባ ዘጠኝ ሺ ዶላር ቅጣት ይጥላል ፈረንሳይ ይህንን ህግ
ለማውጣት ያስገደደኝ የኣንዳንድ ሞዴሎች ክሳት ለጤና አሰጊ በመሆኑ ነው ትላለች::
ለማሰታወቂያ ስራ ሲባል የረባ ምግብ ሳይበሉ የሚገረጡ(ኣነሮግዚክ) የሚሆኑ ግለሰቦችን የሚያበረታቱ ሁሉ ወዮላቸው ይላል ኣዲሱ የፈረንሳይ ህግ::
እንደ ሮይተርስ ዘገባ በፈረንሳይ ከ 30-40 ሺ ሰዎች ከልክ ባለፈ ቅጥነት (ኣነሮግዚያ) ይጠቃሉ::
ጣልያን ስፔን እና እስራኤል ከልክ ያለፈ ቅጥነትን በህግ ካገዱ አገሮች ውስጥ ይገኙበታል