A prolific writer, a well known Ethiopian nationalist and a spiritual mentor for many, Nebure Ed Ermias Kebede passed away .
Nebure ed Ermias is a distinguished writer and intellectual whose books have laid out Ethiopia’s importance to the rest of the world.
በውድ ኢትዮጵያዊነታቸው እና በኢትዮጵያዊነት አቀንቃኝነታቸው የምናውቃቸው ክቡር ኢትዮጵያዊው ሊቅ፣ አባት እና አገር ወዳድ፣ ንቡረ ዕድ ኤርሚያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ ከዚህ ዓለም ተለይተውል።
“ኢትዮጵያ የዓለሙ መፋረጃ”ን እና ሌሎች ከአስር የሚበልጡ መጽሐፍትን በማሳተም ለንባብ ያደረሱ (እንዲሁም ያልታተሙ ሥራዎችም እንዳሏቸው ሳይዘነጋ)፣ በሀይማኖቱም፥ መጽሐፍ ቅዱስን ኢትዮጵያዊ መልክ እና ቅርጽ ለማስያዝ በመድከም የሚታወቁት፥
በመጽሐፍት ከደረሱን ባሻገር፥ Ethiopia The Kingdom of God የሚል ድረ ገጽ ላይ በመጦመር፣ በአኗኗራቸውና በየሁኔታው ኢትዮጵያዊነትን በመተረክ እናውቃቸዋለን። ከመጽሐፍቶቻቸው መካከልም…
1. ምናሴ የመከራየ ደስታ አለምን ረታ 2. Ethiopia: The Classic Case 3. ኢትዮጵያ የዓለሙ መፋረጃ 4. ኢትዮጵያዊው በማንነቱ ፍለጋ 5. ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት (1) 6. ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት (2) 7. ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት (3)
8. ምሥራች! ከእናት ኢትዮጵያ! ለኢትዮጵያ ልጆች ስለኢትዮጵያዊነት። 9. ኢትዮጵያ የዓለሙ መፋረጃ 10. አዳምና ሔዋን በኢትዮጵያ – ፩ 11. አዳምና ሔዋን በኢትዮጵያ – ፪ 12. ለኢትዮጵያ ሕጻናት (የቅዱሱ ኪዳን ሥርዓተ ትምህርት በግዕዝ እና በዐማርኛ) አንደኛ መጽሐፍ
Source adopted from Yohannes Mola ( Face Book)