በቶሮንቶ ካናዳ ነዋሪ የነበረው ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ኣትሌት ፍስሓ ኣበበ በድንገት ከዚ ኣለም መለየት በብዙዎች ዘንድ ድንጋጤን ፈጥሯል :: የሁሉ ወዳጅ የሁሉ ታዛዥ ነበረ ይላሉ የቶሮንቶ ነዋሪዎች ስለ ፍስሐ ሲናገሩ ፥ ፥ ሰውን መርዳት የማይደክመው ሲሉም ይገልጹታል ኢትዮጵያዊው አትሌት ፍስሐ አበበ ባለፈው ማክሰኞ ነበር ከዚህ አለም በሞት የተለየው::
ፍሰሐ እ።ኤ።አ ማርች 20/1983 ታላቋ ብሪታንያ ጌጽሄድ ከተማ ባዘጋጀችው 11ኛው የአለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ተወዳድሮ የወርቅ ሜዳልያ ለሃገሩ ከማስገኘቱም በላይ በቀጣዩ አመት ኒውዮርክ ሲቲ በተዘጋጀው 22 ኛው የአለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ ሃገሩን መወከል ችሏል ሲል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኣውስቷል ::
ፌዴሬሽኑ ለአትሌት ፍሰሐ አበበ ቤተሰቦችና ለአድናቂዎች መጽናናት ተመኝቷል::