ቶሮንቶ ተደምራለች
የቶሮንቶ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በ ቅርቡ ወደ ስልጣን በ መጡ በ ኣጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ለውጦችን ያስመዘገቡትን የ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ኣብይ ኣህመድን በመደገፍ ደማቅ ሰልፍ ኣካሄዱ፤፤
Ethiopian Canadians held a rally in support of the newly appointed Ethiopian Prime minister ABiy Ahmed . At a rally filled with love , passion and national feelings,Several hundreds of Toronto residents of Ethiopian origin show their love and support to the prime minster at a rally held on Danforth street . Faith leaders and other speakers emphasized the need to be united and condemned divisions along the lines of ethnicity. The Toronto task force, one of the most vibrant socio- political justice movements in Toronto organized the rally.
የቶሮንቶ ግብረ ሃይል ያዘጋጀው የ መደመር ቀን ላይ ይቅርታን ፍቅርን እና ኣንድነትን የሚያጎሉ መፈክሮችን ይዘው የወጡ ኢትዮጵያውያን የፍቅር ጊዜ ኣሳልፈዋል ፥፥ በስነስር ኣቱ የተገኙ የሃይማኖት ኣባቶች እና ሌሎች ተናጋሪዎች ኢትዮጵያውያንበ ዘር በሃይማኖት እና ሌሎች ልዩነቶች ሳይከፋፈሉ ኣንድነታቸውን ኣጠናክረው እንዲቀጥሉ ኣሳስበዋል
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚ ሳምንት በ ዳያስፖራ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከ ኣንድ ዶላር ጀምሮ በማዋጣት በ ኣገራችን እድገት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል ፥፥
ቶሮንቶ በ ብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩባት ከተማ ናት በተለይም ዳንፎርዝ እና ብሉር የተባሉ ጎዳናዎች ላይ በርካታ የ ኢትዮጵያውያን ንግድ ተቋማት ይገኛሉ ።
ሰልፉን ያስተባበረው የ ቶሮንቶ ግብረ ሃይል ከ ዚ ቀደም በ ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማህበረሰቡን በማንቀሳቀስ ድምጹን ሲያሰማ ቆይቷል
Photos by Ethiopians in Toronto Facebook