How to Deal with Holiday Related Stressየበዓላት ውጥረትን ለመቀነስ

በዓላት የደስታ ቀናት ናቸው ከቤተሰብና ከጓደኛ የሚገናኙበት፣ የደስታ ቀናት ናቸው። ሆኖም አስጨናቂ ሊሆኑም ይችላሉ። በበአላት ቀናት ስጦ ታ መስጠትና ገበያ መገብየት ከፍተኛ ጫና ሊፈጥርብዎት ይችላል። የገንዘቡ ሁኔታ አሳሳቢ ሊሆን ይችላል፣ የበዓል ቀናት በራሳቸው አታካችም ሊሆኑ ይችላሉ። በዚህም ምክንያት የሚፈልጉትን ነገሮች ለማድረግ በቂ ጊዜና አቅም ሊያጥርዎት ይችላል።

Photo by Yohannes Ayalew-ethiofidel.com

በበዓል ቀናት ለጭንቀት የሚዳርጉ ክስተቶችን አስቡት። ስለዚህ ሊያደርጓቸው በሚችሏቸው ከሁለት ያልበለጡ ነገሮች ብቻ ላይ ማተኮር ጭንቀትዎን ለመቀነስ ይረዳል።

ለበዓላት ቅድመ ዝግጅት ማድረግ

  • የወጪ አቅምዎን ይወቁ

የገንዘብ ዕጥረት በበዓላት ቀን ለሚፈጠሩ ውጥረቶች ዋነኛው መንስኤ ሊሆን ይችላል። በዚህ አመት ወጪዎን ይተምኑ: ካቀዱት ውጭ ላለማውጣት ይሞክሩ። ለልጅዎ አንዳንድ መጫዎቻዎች ውድ መሆናቸውን መንገር ምን አይደለም። የሚገዙት ስጦታ አዲሱን ዓመት ሲከፍሉት የሚኖሩት ዕዳ እንዳይሆንብዎት ይጠንቀቁ።

  • ስጦታዎችዎ ልባዊ ይሁኑ  ልባዊ ስጦታዎች አሳቢነትን፣ መውደድዎን ስለሚያሳዩ ስጦታው የሚሰጠው ሰው ለርስዎ ምን ማለት እንደሆነ የሚገልፁ ቃላቶች ከሚገዙት ውድ ዕቃ ይልቅ ይበረክታሉና ልባዊ የሆኑ ስጦታዎችን ይስጡ።
  • ራስዎን ያዘጋጁ በበዓላት ቀን ለማድረግ የሚያስቡትን ነገሮች ዝርዝር ይፃፉና በዝርዝሩ መሰረት ያድርጉ። ቀጠሮ ካለዎት፣ የተጋብዙባቸው ቦታዎች ከአንድ በላይ ከሆኑ፣ ዝርዝሮችን መፃፍዎ ባለቀ ሰዓት የሚፈጠሩ ውጥረቶችን ይቀንስልዎታል።
  • ሥራ ያካፍሉ። ሁሉንም ነገር ለብቻዎ ለማድረግ አያስቡ። ለቤተሰቦችዎ ሥራ ያከፋፍሉ። ስጦታ መጠቅለል፣ ቤት ወይንም ምግብ ማዘገጃጀትና የመሳሰሉትን ሥራዎች ያከፋፍሉ።
  • ሁሉንም እሺ አይበሉ  አንድዳንዴ እሺ በማለት ግብዣዎችን ሁሉ የሚቀበሉ ከሆነ የርስዎንም የጠሪዎንም ቀን ያበላሻሉ። በጣም አስፈላጊ ግብዣ ብቻ ይቀበሉ እንጂ ሁሉንም ጥሪ አይቀበሉ።
  • ከእውነታው አይውጡ . በዓሉን ፍፁም ለማድረግ ሲሉ በራስዎ ላይ  አላስፈላጊ ጫና አይፍጠሩ።ወዳጆችዎ መሰባሰባቸው እና መጫወታቸውን እንጂ እንከን የለሽ በዓል እንዲሆን አይጨነቁ።

በበዓላት ቀናት / የበዓሉ ዕለት

በበዓል ቀን ውጥረቶችን መቀነስ ወይንም ማስወገድ አይችሉም ይሆናል። ሆኖም ነገሮችን ጤናማ በሆኑ መንገዶች ለመፍታት ያቅዱ።

  • በበዓሉ ቀን ለራስዎ ጊዜ ይፈልጉ።   በበዓሉ ቀን እርስዎ ምን ምን አይነት ስሜት እንዳለዎትና ምን እንደሚፈልጉ ይወቁ። ለአጭር ደቂቃም ቢሆን ለብቻዎ ጊዜ ያግኙ። ለግል ፀሎት፣ አጭር ሽርሽር(ዎክ) ዘና የሚያደርግዎት አጭር ዕንቅልፍ ወይንም ጥልቅ ትንፋሽ ለማድረግ ጊዜ ይፍጠሩ። 
  • መደበኛ የምግብ፣ የዕንቅልፍ እና የስፖርት ጊዜዎን አያስተጓጉሉ፣ የሚወስዱትን የአልኮል መጠን ይቆጣጠሩ።  ራስዎን መንከባከብዎ በበዓላት ወቅት ለሚፈጠር ውጥረት የሚያደርጉትን ለመቆጣጠር ያስችልዎታል።
  • ዕርዳታ ያስፈልግዎት ይሆናል።  የቅርብ ሰው በዛ በበዓል ቀን በሞት፣ ወይንም በፍቺ፣ አጥተውት ከሆነ በዓሉ ላይ ተጨማሪ ጫና ፈጥሮ ወደ ጭንቀት ሊቀየር ይችላል። በዚህ ሁኔታ ላይ ካሉ ዕርዳታ ለመጠየቅ ማፈር የለብዎትም። ወይንም ግዴለም እችለዋለሁ፣ እወጣዋለሁ ብለው ያስቡት ይሆናል። ሆኖም ሐኪም ይማክሩ፣ ከሚያስቡት የበለጠ ነገሮች ይቀልልዎታል። Source Health Link BC – Written by Leul Dawit

Yohannes Ayalew

Related Posts

Leave a Reply

Read also x