Ethiopia issues new currency bills. The country is replacing the existing 10, 50 and 100 Birr notes with new ones . Prime minister Abiy Ahmed said that the new measures are necessary to salvage the economy by protecting fraud, hoarding and counterfeit.
According to the changes , there will be an additional bill of 200 Ethiopian Birr. According to Ethiopian news Agency , people have 3 months window period to change to the new bills and in the transition both the old and new bills can be used .
አዲሱ የብር ኖት 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ታትሞ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ለስርጭት ዘግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ።
ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ኖቶች በመተካት አዲስ የገንዘብ ኖቶች እንደሚጀ መር ይፋ ተደርጓል:: ይህም አዲሱን የ200 ብር ገንዘብ ይጨምራል ::
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ አዲሱን የብር ኖት በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም አሁን ላይ 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ታትሞ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች የብር ኖት ቅያሬውን ለማከናወን ዝግጅቱ መጠናቀቁን ገልጸዋል።
አዲሱን የብር ኖት ለማሳተም 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ውጭ መደረጉንም ገልጸው፤ በሁሉም ክልሎች በበቂ ሁኔታ ለማድረስ ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል። የብር ቅያሬው በውክልና የማይከናወን በመሆኑ መታወቂያ በመያዝ ባለቤቱ ብቻ ማከናወን ይኖርበታል ብለዋል።
ከአጎራባች አገራት የሚገባን ህገ ወጥ ገንዘብ ለመቆጣጠር በድንበር አካባቢ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግ መሆኑንም ዶክተር ይናገር ገልጸዋል።
Source Tikvah Ethiopia