Ethiopia Completed The Second Round Filling of the Reneisance Dam

Ethiopia announced that it has completed second round filling of its huge dam on Nile .

ዛሬ ሀምሌ 12ቀን 2013 ዓ.ም የሁለተኛው አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ ፈሷል:: ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችም እንኳን ደስ አላችሁ።

The project head of the Grand Ethiopian Renaissance Dam, GERD, Sileshi Bekele announced that the filling has been completed and water is overflowing .

“The 2nd round filling of our flagship project – the GERD has been completed. The dam’s two turbines will soon generate electric power. Congratulations Ethiopia.” says Bekele sin a statement.

ግድቡ ተሞልቷል

ይህ ውጤት ማለት 2 ተርባይኖችን ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልገውን የውሃ መጠንና ይዘናል ማለት ነው::
በዘንድሮው አመት እየዘነበ ያለው ውሃ መጠን እጅግ ከፍተኛ ነው። ይህም ከፈጣሪ የተሰጠን ፀጋ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነና እንዴት እያገዘን እንደሆነ መረዳት እንችላለን:: ለዚሁም ምስጋና ይግባው!

የግድቡ ፕሮጀክት አስተባባሪ ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እዚህ ደረጃ ለመድረስ በዘንድሮው አመት መጠነ ሰፊ ስራ ሰርተናል:: በቀጣይ ሁለቱ ተርባይኖች እንዲያመነጩ ብርቱ ስራዎች እየተሰሩ ነው እናም ያንን በቅርብ ወራት በማጠናቀቅ ልፋታችንን ውጤት ላይ እናደርሳለን ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

Yohannes Ayalew

Related Posts

Leave a Reply

Read also x