Ethiopoans across the globe are mourning the death of their music legend .Alemayehu Eshete, considered the jwel of Ethiopia’s modern music died of a heart attack yesterday .
አንጋፋው ኢትዮጵያዊ ድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ከዚ አለም በሞት ተለይቷል።
አርቲስት አለማየሁ በድንገተኛ የልብ ህመም የተነሳ ማረፉን ኢቢሲ ዘግቧል።
Ethiopian broadcasting Corporation (EBC) reported Alemayehu was returning from his regular job and had a heart pain. He was taken to hospital where he later passed away.
Nicknamed “The Elvis Presley of Ethiopia” Alemayehu Eshete was a trendy singer with passionate stage appearances that turned him in to a legend in Ethiopia’s music industry.
የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ እንቁዎች ውስጥ አንዱ የሆነው አለማየሁ እሸቴ ለበርካታ አመታት ያበረከታቸው ዘፈኖች ትውልድ ተሻጋሪ ሆነው ቆይተዋል።
አለማየሁ እሸቴ የኢትዮጵያን ዘመናዊ ሙዚቃ ከፍ ወዳለ ደረጃ ካደረሱት አንዱ ነው “ኢትዮዽያዊው ኤልቪስ” በመባልም ይጠራ ነበር ።
“አዲስ አበባ ቤቴ” ምሽቱ ደመቀ፣ እንደ አሞራ :ተማር ልጄ “የወይን አረጊቱ” ችግርሽ በኔ አልፏል የሚሉት ዘፈኖቹም ከተወዳጅ ሙዚቃዎቹ መካከል ይገኙበታል:;
አለማየሁ ከሸክላ እስከ ሲዲ እንዲሁም ኢትዮፒክስ በተስኙ አልበሞች አማካይነት በርካታ የሙዚቃ ስራዎችን አበርክቷል ።
በአለም ዙሪያ ያሉ የሙዚቃ አፍቃሪያን ኢትዮጵያ ትልቅ የሙዚቃ ሰው አጣች ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል ።
በኢትዮጵያ የግል ሸክላ ሙዚቃ ህትመት ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ የሆነበትን ሙዚቃ በአምሃ ሬከርድስ አማካኝነት ያሳተመ የዘመናዊ ሙዚቃ ባለሙያ ነበር አለማየሁ እሸቴ።
አለማየሁ እሸቴ ከቅርብ ግዜ በፊት በቶሮንቶ ካናዳ ዝግጅቱን አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል።