Canada Public Public Health Agency of Canada Confirms 2 cases of Monkeypox . The agency is still investigating the cases .
Monkeypox is a zoonotic infectious disease found in parts of central and West Africa that result in occasional human infections usually associated with exposure to infected animals or contaminated materials. Limited cases have been identified in other regions in the past, including the United Kingdom, United States, Israel and Singapore, but never before in Canada. For the recent international cases, it is not yet certain how the individuals were exposed to monkeypox virus.
ከሰሞኑ በ ካናዳ በዩናይትድ ኪንግደም፣ ፖርቱጋል፣ ስፔን እና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የጦጣ ፈንጣጣ (Monkeypox) ተከስቷል።
ለመሆኑ የበሽታው መገለጫዎች ምንድናቸው ?
የጦጣ ፈንጣጣ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ ሲሆን ብዙውን ጊዜ ቫይረሱን የሚሸከሙ እንስሳት ባሉበት ሞቃታማ የዝናብ ደኖች አቅራቢያ ይገኛሉ።
የጦጣ ፈንጣጣ የሚጀምረው ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የጡንቻ ሕመም ፣የንፍፊት እብጠት፣ ብርድ ብርድ ማለት እና ድካም ያሳያሉ።
ትኩሳት ከታየ ከ 1 እስከ 3 ቀናት ውስጥ (አንዳንዴ ረዘም ያለ ጊዜ) በሰዉነት ላይ ሽፍታ ይወጣል። ብዙውን ጊዜ ሽፍታዉ ፊት ላይ ጀምሮ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ይስፋፋል። በአጠቃላይ በሽታው ከሁለት እስከ አራት ሳምንታት ይቆያል።
የጦጣ ፈንጣጣ (Monkeypox) በተወሰነ መልኩ ከፈንጣጣ በሽታ ጋር ተመሳሳይነት አለዉ ። ነገር ግን በፈንጣጣ እና የጦጣ ፈንጣጣ ምልክቶች መካከል ያለው ዋነኛው ልዩነት የጦጣ ፈንጣጣ የንፍፊት እብጠት ሲያመጣ ፈንጣጣ አያመጣም።
ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው ስርጭት የተገደበ ቢሆንም ከሰውነት ፈሳሾች ጋር በመገናኘት ፣ በቆዳ ላይ ወይም በውስጣዊ ንጣፎች ላይ ለምሳሌ በአፍ ወይም በጉሮሮ፣ በመተንፈሻ አካላት ጠብታዎች እና በተበከሉ ነገሮች ላይ ሊተላለፍ ይችላል።
የቀድሞ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአፍሪካ የጦጣ ፈንጣጣ በበሽታው ከተያዙት ከ10 ሰዎች ውስጥ 1 ሰዉ ላይ ሞት እንደሚያደርስ ታይቷል።
በትላንትናው እለት እስራኤል እና ስዊዘርላንድ የመጀመሪያዉን የጦጣ ፈንጣጣ (Monkeypox) በሽታ ሪፖርት አድርገዋል።
ባለፉት ሳምንታት በእንግሊዝ፣ በፈረንሳይ፣ በጀርመን፣ በቤልጂየም፣ በጣሊያን፣ በፖርቹጋል፣ በስፔን እና በስዊድን እንዲሁም በአሜሪካ፣ በካናዳ እና በአውስትራሊያ ከ100 በላይ የጦጣ ፈንጣጣ በሽታ(Monkeypox) መገኘቱን ተከትሎ ቫይረሱ ሊስፋፋ ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።
ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ቫይረሱ በሌለባቸው አገሮች ውስጥ ያለው ወረርሽኝ ያልተለመደ እንዲሁም የአሁኑ የጦጣ ፈንጣጣ(Monkeypox) ዝርያ የሚለየዉ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች ሊሆን እንደሚችል እየተገለፀ ይገኛል።
የዓለም ጤና ድርጅት በበሽታው ከተጠቁ ሀገራት እና ከሌሎች ጋር በመሆን የበሽታ ክትትልን በማስፋት የተጠቁ ሰዎችን ለማግኘት እና ለመደገፍ እንዲሁም በሽታውን እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል መመሪያ ለመስጠት እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።
የዝንጀሮ በሽታ ከኮቪድ-19 በተለየ ሁኔታ ይተላለፋል። ሆኖም ግን በንክኪ ከሰዉ ወደ ሰዉ ሊተላለፍ ስለሚችል ጥንቃቄ ይሻል ።
እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ገለፃ በሚቀጥሉት ሳምንታት ከተለያዩ የአዉሮፓ ሀገራት የጦጣ ፈንጣጣ በሽታ ሪፖርት ሊኖር እንደሚችል ገልጿል።
(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)
ምንጭ: tikvah ethiopia, Public health Agency of Canada