February is a Black History Month in North America. We celebrate achievements of notable black people and the community at large
ፊብሩዋሪ በሰሜን አሜሪካ የጥቁር ህዝቦች ታሪክ ወር ነው። የታዋቂ ጥቁር ህዝቦች እና የማህበረሰቡ ስኬቶች ይወሳሉ፡፡ ታሪክን እያወሱ ለጥቁር ማህበረሰብ አባላት ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት እድል የሚፈጥር ወቅት ነው ፡፡
በቶሮንቶ መሃል ከተማ በተካሄደ የጥቁር ማህበረሰቦች ጤና እና ደህንነት ዝግጅት ላይ በታወቁ ጥቁር ሳይንቲስቶች የ ተገኙ የፈጠራ ስራዎችን የሚያሳየውን አነስተኛ ኤግዚቢሽን ቀርቧል ፡፡ በተለይ አንድ ፎቶ ትኩረታችን አግኝቷል፡፡ የኢትዮጵያዊው የ ሽፈራው ዶሾ ፎቶ።
አቶ ሽፈራው እ.ኤ.አ. በ2014 ከዚህ አለም በሞት የተለዩ ኢትዮጵያዊ የምርምር ግኝት ባለቤት እና ስራ ፈጣሪ ነበሩ።ሽፈራው ቦውፍሌክስ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማሽንን በዩናይትድ ስቴትስ በመስራት ለአሜሪካውያን በማቅረብ ይታወቃሉ ፡፡
በ17 አመታቸው 500 ዶላር ብቻ ይዘው ወደ አሜሪካ የገቡት ፣ አቶ ሽፈራው ተስፋ አስቆራጭ በሆነ መልኩ የፈጠራ ስራ እቅዶቻቸው በተደጋጋሚ ውድቅ ቢደረጉባቸውም ቦውፍሌክስ የተሰኘውን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማሽን በመስራት የፈጠራ ባለቤትነት በተሳካ ሁኔታ ያገኙ እና ለሌሎችም ስራን የፈጠሩ ታታሪ ግለሰብ ነበሩ ፡፡
ወደ አሚሪካ በመጡበት ወቅት ቤተሰብ ለማስተዳደር ሌሎች ስራዎችን እየሰሩ በጎን ደግሞ ይህንን የ ቦውፍሌክስ ስፖርት መስሪያ ማሽን ፈልስፈዋል ፡፡ በማንኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢያልፉም አቶ ሽፈራው የራሳቸውን ብራንድ የመፍጠርን ትልቅ ራእይ አልዘነጉም፡፡
በኤግዚቢሽኑ ላይ በተጻፈው ማስታወሻ መሠረት፣ የ ተመራማሪ ሽፈራው ፈጠራ ቦውፍሌክስ ማሽን በ1996 በአሜሪካ የፋይናንስ አክሲዮን ልውውጥ ውስጥ ዋነኛ ተወዳጅ ዕቃ ሆኖ ነበር ፡፡ ከ 20 በላይ የሚሆኑ ፓተንቶችም ነበራቸው፡፡
ብዙዎች የተስተካከለ የአካል ብቃት እንዲኖራቸው የሚረዳውን በቀላሉ ቤት ውስጥ መጠቀም የሚቻለውን የምርምር ውጤት ያበረከቱት ኢትዮጵያዊው ሽፈራው ዶሾ በካናዳ ዝግጅቶች ላይ በቀረበው ዝግጅት ባሻገር ታሪካቸውን በሰሙ ወገኖች ዘንድም ይታወሳሉ፡፡
ኢግዚቢሽኑን ያሳዩት እና የ አፍሪካ አሜሪካ እና ጥቁር ካናዳውያንን የፈጠራ ስራዎች የሚዘክሩትን ድርጅቶች ድረገጽ በመጎብኘት ሊሎች ፈጠራ ያበረከቱ ግለሰቦችን የበለጠ ማወቅ ትችላላችሁ https://multiculturalmuseums.org/ .
Attending a Black health and wellness event downtown Toronto, I noticed an exhibit of prominent inventions by Black scientists.
One picture in particular was of an interest . The picture of Dosho Shiferaw piqued my curiosity.
Shiferaw was an Ethiopian inventor and entrepreneur who passed away in 2014. Shiferaw invented the Bowflex exercise machine in the united states and was known for his essential inventions for American household use.
Landing in the United States with just $500 at the age of 17, Shiferaw successfully patented an invention of the exercise machine called Bowflex after several discouraging rejections.
While having to work to support his family, Shiferaw never took gaze away from his grand vision of creating his own brand.
According to the exhibit notes, Shiferaw’s invention, Bowflex became a fast selling item in America’s financial market back in 1996.
An Ethiopian with a great contribution of helping people in getting to a great shape is well remembered
Check out the exhibitors from Multicultural Inventors Exhibit at https://multiculturalmuseums.org/