This team represented Toronto at the soccer and culture festival hosted by The Ethiopian Sports Federation in North America (ESFNA) for 40 years . Great Milestone to celebrate . Ethio Star of Toronto celebrated its 40 years anniversary this weekend at Lalibela Ethiopian Restaurant on the Danforth .
የቶሮንቶው የ ኢትዮ ስታር የ እግር ኳስ ቡድን 40 ኛ አመት በአሉን አከበረ::
በ የአመቱ በሚካሄደው የ ሰሜን አሜሪካ ኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ እና የባህል ፌስቲቫል ላይ ላለፉት 40 አመታት ቶሮንቶን ብሎም በ ካናዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በመወከል የተሳተፈ የስፖርት ቡድን ነው
ትላንት በ ላሊበላ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት በ ዳንፎርዝ በተደረገ ስነስርአት ላይ የቡድኑ መስራች አባላትን ጨምሮ የ ቡድኑ አመራሮች እና ወዳጆች ተገኝተዋል፡፡
የኢትዮ ስታር የ እግር ኳስ ቡድን የቦርድ ሊቀመንበር የሆነው እና ታዋቂው የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች አሸናፊ ግርማ የ ቡድኑ አመራሮች ደጋፊዎች የማህበረሰቡ አባላት እና ሌሎችም ለቡድኑ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርቧል ፡፡
ኢትዮፊደልን ጨምሮ ሌሎች የማህበረሰብ ሚዲያ አባላትም የተዘጋጀላቸውን የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል ስትል ባልደረባችን ጽናት ብርሃኑ ዘግባለች::
የኢትዮ ስታር የእግር ኳስ ቡድን የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን በ ሰሜን አሜሪካ ከተቋቋመ አንስቶ ላለፉት 4 አስርት አመታት በመሳተፍ እና በአብሮነት በመቆየት ይታወቃል::
በዚሁ ዘመናት ውስጥ ይህን ቡድን በማሰልጠን በማስተባበር እንዲሁ በተለያዮ ጊዜ በመሪነት ከምስረታው ጀምሮ አስተዋጽኦ ያደረጉ አንጋፋ አባለትም የእውቅናና የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰቷቸዋል::
በዚህም ወቅት ልምዳቸውንን እና ገጠመኛቸውን አካፍለዋል በቀጣይም ለቡድኑ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንደሚቀጥሉ ነው ያረጋገጡት፡፡
በዘህም አመት ከ june 29-July 06,2024 በሚካሄደው ውድድር ላይ የሚሳተፈው ቡድን አባላት የእራት ግብዣ አና ማበረታቻ ተደርጎላቸዋል ።
The club’s board chair and the famous Ethiopian National Team player Ashenafi Girma acknowledged the contributions of the founding members, coaches, players and the community .
Ashenafi attributed the success of the team to the unwavering support from the community members, businesses, individuals and media outlets .
A certificate was presented at the ceremony to all that supported the team through out the years Ethiofidel has been recognized for its support towards the activities of the Ethio star soccer team . Ethiofidel would like to thank the Board of Directors of Ethio Star Team for the certificate and recognition.
According to the report by Tsenat Berhanu, Ethio Star will take part in this years ESFNA from June 29-July 06,2024 in Atlanta .
Photos and additional information by Etsubdink Lealem