Five Ways to Keep Your Kidneys Healthy

ለጤናማ ኩላሊት ማድረግ ያለብን አምስት ልምምዶች

ጤናማ ኩላሊትን መጠበቅ ለአጠቃላይ ጤንነት አስፈላጊ ነው። የኩላሊቶቻቸሁን ጤንነት ለመጠበቅ የሚያግዙ

አምስት ቁልፍ ምክሮች እነሆ፡-

1. መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፡ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ ተጋላጭነትን ይቀንሳል። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የደም ግፊትን ለመቀነስ እና የልብ ጤናን ያጠናክራል፣ ሁለቱም የኩላሊት ጉዳትን ለመከላከል ወሳኝ ናቸው። እንደ የ እግር ጉዞ ማድረግ፣ መሮጥ፣ ብስክሌት መንዳት ወይም ዳንስ ያሉ እንቅስቃሴዎች ጠቃሚ ልምዶች ናቸው።

2. የደም ግፊት መጠንን እየተከታተሉ መለካት ከፍተኛ የደም ግፊት የኩላሊት ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። ጤናማ የደም ግፊት  120/80 mm Hg ወይም ከዚያ በታች ነው። የደም ግፊትዎን በመደበኛነት መለካት እና በአኗኗር ዘይቤ ለውጦች ወይም መድሃኒቶች በዚህ ክልል ውስጥ እንዲቆይ ማድረግ ኩላሊዎን ከበሽታ ይጠብቃል።

3. የተመጣጠነ ምግብን ይመገቡ፡ በፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ጥራጥሬ እና ቅባት ፕሮቲኖች የበለፀገ ምግብን መመገብ የኩላሊት ጤናን ይደግፋል። ሶዲየም፣ፕሮሰስድ ስጋ እና ሌሎች ኩላሊትን የሚጎዱ ምግቦችን መቀነስ ጠቃሚ ነው። እንደ አበባ ጎመን፣ ብሉቤሪ እና ዓሳ በመሳሰሉት በተፈጥሮ ዝቅተኛ የሶዲየም ንጥረ ነገር አላቸውን ምግቦች ያዘውትሩ።

4.  በቂ ውሃ መመውሰድ፡ በቂ ውሃ መውሰድ ሶዲየም እና መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ከኩላሊት ለማጽዳት ይረዳል። የእያንዳንዱ ግለሰብ የሚያስፈልገው የውሃ መጠን ቢለያይም፣ በየቀኑ ወደ 1.5 ሊትር (በግምት 8 ኩባያ) ውሃ መጠጣት ይመከራል ። ድብዘዝ ያለ ቢጫ ሽንት የውሃ እጥረት( Dehayrdation) ሊያመለክት ይችላል::

5. ማጨስን ያስወግዱ እና አልኮልን ይገድቡ፡- ሲጋራ ማጨስ የደም ሥሮችን ይጎዳል፣ ወደ ኩላሊት የደም ዝውውርን ይቀንሳል፣ አልኮሆል ከመጠን በላይ መውሰድ ደግሞ ለደም ግፊት ይዳርጋል። ማጨስን ማቆም እና አልኮልን በመጠኑ መጠጣት የኩላሊትን ጤንነት ለመጠበቅ ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው።

እነዚህን ልምዶች በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎ ውስጥ ማካተት ለኩላሊት ጤና ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል።

ይህ ካነበብነው ያካፈልናችሁ ነው፡፡ የኩላሊትም ሆነ የ አጠቃላይ ጤናዎን ለመጠበቅ ዶክተርዎን ማማከር አስፈላጊ ነው

ምንጮች ፡ Health line Canada

             Health Canada

National Kideney Foundation

Yohannes Ayalew

Related Posts

Leave a Reply

Read also x