Ethiopian Association in GTA In Solidarity with PM ABiy Ahmed’s Reforms in Ethiopia

The Ethiopian Association in GTA and Surrounding Regions expressed its solidarity with the reforms by the recently appointed Prime Minister of Ethiopia, Dr. Abiy Ahmed . In a press release sent to ethiofidel.com, the Ethiopian Association in Toronto appreciated the recent reforms under the new leadership of Prime Minister Abiy . The press release recalled the human right abuse and the luck of democracy in the country for the past 40 years in the country and called up on all Ethiopians to stand with Prime Minister Dr. Abiy Ahmed . This is to bring about change in Ethiopia where every one’s human rights have been respected with our ethnic division. 

The Association also condemned the grenade attack during the mass rally in Addis organized in support of Dr. Abiy Ahmed on June 23, 2018 . 

Here is the full Pres release in Amharic . 

Click the link below .

Ethiopian Association Press Release

የኢትዮጵያ ማህበር በቶሮንቶና አካባቢው Ethiopian Association in the GTA and Surrounding Regions

ከኢትዮጵያ ማህበር በቶሮንቶና አካባቢው የተሰጠ መግለጫ

ቅዳሜ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓም በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር የኢትዮጵያ ሕዝብ በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ላይ በመውጣት በዶክተር አቢይ አህመድ አመራር እየተካሄደ ያለውን የአንድነት፣ የፍቅርና የሰላም ለውጥ በመደገፍ ምስጋናውን የገለጸበትን ሰላማዊ ሰልፍ.፡ የኢትዮጵያ ማኅበር በቶሮንቶና አካባቢው ደስታውንና ድጋፉን መግለጽ ይወዳል።

ይህን የሰላም ለውጥ በፍቅርና በደስታ ስሜቱን ሲገልጽ የነበረው ሕዝብ ላይ በጸረ ሰላምና ጸረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ወይም ቡድኖች በተወረወረ ቦምብ የሰዎች ሕይወት ጠፍቷል፣ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ቆስለዋል። የኢትዮጵያ ማሀበር በቶሮንቶና አካባቢው ይህን አረመኔ ድርጊት በጽኑ እያወገዘ፤ በሞት የተለዩትን ስዎች ቤተስቦች ፈጣሪ መጽናናትን ይሰጥልን ዘንድ እየተመኘ፤ የቆሰሉትን ደግሞ ምሀረቱን እንዲሰጣቸውና ድነው ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው እንዲመለሱ ምኞቱን ይገልጻል።

ላለፉት አርባ አራት ዓመታት አስተማማኝ ለውጥ ለማምጣት ብዙ ጥረት እየተደረገ እስከዛሬ ድረስ ትክክለኛና ሕግ ተከትሎ በሕዝቡ ፍላጎት የሚሄድ አመራር ቢናፈቅም ሊሳካ ሳይችል ቆይቷል። ላለፉት ብዙ ዓመታት በአገራችን የሕግ የበላይነት ባላመከበሩ፤ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በመካሄዳቸው፣ ብዙዎች ወገኖቻችን ሕይወታቸው አጥተዋል፣ ለስደት ተዳርገዋል፣ በእሥር ተሰቃይተዋል ሌሎችም ከፍተኛ መስዋዕትነት ቢከፍሉም የነበረው ሁኔታ ፍጹም ሊሻሻል አልቻለም ነበር።

ዛሬ ደግሞ ዶክተር አቢይ በአዲስ አስተሳሰብና አመራር ትልም እያሳዩ በመሆናቸው በአገሩም ውስጥ ሆነ በውጭ ያለን መላው የአገራችን ሕዝብ ከጎናቸው በመቆም ልናግዛቸውና ልንተባበራቸው ይገባል። በዚህም አካሄድ ደግሞ አገራችን እንደወትሮው በሕግ በነፃነትና በኩራት የሰው ኅልውና መብት የሚከበርባት፤ የዘር፣ የሐይማኖት ወይም ሌላ ልዩነት ሳይደረግ ሰዎች በእኩልነት ተባብረው የሚኖሩባት ዲሞክራሲያዊት አገር እንድትሆን ለማድረግ ብዙ ጥረት ይጠበቅብናል።

የጥንት አባቶቻችን ከማንም ያልወሰዱት የራሳቸው የሆነ ሥልጣኔ፣ የራሳቸው ባሕል፣ የራሳቸው ሐይማኖት፣ የራሳቸው ሥርዓት፣ የራሳቸው ሥነጽሁፍና ፊደላት፣ የራሳቸው አለባበስ፣ የራሳቸው አበላልና አጠጣጥ የነበራቸው ሰዎች ነበሩ። ለዚሁም በአገራችን የሚገኙት የታሪክ ቅርሶቻችን ምስክሮች ናቸው። ከዚህም በላይ ጥቃት የማይወዱ በመሆናቸው ከሚመጣው ጠላት ሁሉ እየታገሉ ባሸናፊነት የራሳቸውን ነፃነት አስከብረው በኩራት የኖሩ ናቸው። መጪውም ትውልድ ተረካቢ በመሆኑ ወጣቱ ኃላፊነት እየወሰደ የእነሱን አርአያነት በመከተል የአገሩን ክብር በታላቅ ሞራል በታሪኩ ኮርቶ ወደፊት በተሻለ ለመምራት ዝግጁ መሆን ይጠበቅበታል።

“አንደነት ኃይል ነው”

የኢትዮጵያ ማሀበር በቶሮንቶና አካባቢው

 

Yohannes Ayalew

Related Posts

Leave a Reply

Read also x