A thanksgiving festival of the Oromo tribe in Ethiopia was celebrated in Addis Ababa today . This year, the Irreecha festival was celebrated with limited number of participants due to COVID-19.
አመታዊዉ የኢሬቻ በአል በአዲስ አበባ በሆራ ፊንፊኔ ተከብሯል ። የኦሮሞ ህዝብ የምስጋና ቀን የሆነው ኢሬቻ በዚህ አመት በኮረና ምክንያት በጥቂት ተሳታፊዎች ነው የተከበረው ። የበዓሉ ስነ ስርዓት የተጀመረው በገዳ ሥርዓት መሰረት በአባገዳዎች ምርቃት ነው፡፡
ባህላዊ የኦሮሞ አልባሳትን ያደረጉ የበአሉ ተሳታፊዎች ለፈጣሪ ምስግና አቅርበዋል ስላምንም ለምነዋል።
በበዓሉ ላይ ለመታደም ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ሆራ ፊንፊኔ በማቅናት በባህሉ መሰረት ለፈጣሪያቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ፋና እንደዘገበው ከአዲስ አበባ እና ከዙሪያዋ እንዲሁም ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ለበዓሉ በባህል አልባሳት ደምቀው በሆራ ፊንፊኔ በመገኘት ኢሬቻውን በአንድነት መንፈስ በጋራ አክብረውታል፡፡
Crowds from all over the country with colorfull traditional Oromo attire graced the event in the Ethiopian capital Addis Ababa.
Annualy , the Oromo people around the world celebrate Irreecha that marks the end of the rainy season and the beginning of the harvest season.
Irreech, a UNESCO registered heritage and one of the largest festivals in Africa typically attracts hundreds of thousands of people.
According to Ethiopian News Agency , the participants praised Waaqaa(God) led by Oromo traditional leaders .