A virtual frum on mental health will be carried out in the coming months . Organizor Tseday Legesse informed ethiofidel.com that the virtual Zoom meeting is aimed at opening up a dialogue about mental health with in the communities .
“ያለ ዓዕምሮ ጤና፡ ምን ህይወት አለና” በሚል መሪ ቃል የተለያዩ መንፈሳዊና ሳይንሳዊ ምሁራን የሚሳተፉበትና ከተመቻችሁ ቦታ ሆናችሁ የምትካፈሉበት የዙም (zoom) ላይ ዓውደ ጥናት ሊቀርብላችሁ ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ ነው::
Mental Health is one of the crucial topics in our communities . There is a planned Zoom meeting in Toronto for the communities . Here is a message from the organizers :
ውድ ወገኖቻችን ሰላም ለሁላችሁም ይሁን! በወቅቱ የተከሰተብንን አስቸጋሪ ሁኔታ በትዕግሥትና በብልሃት ለማለፍ ሁላችንም በየበኩላችን በምናደርገው ጥረት የኑሮው ክብደትና የማህበራዊ መራራቁ መዘዝ
አካላዊና መንፈሳዊ ጫና (Stress, Depression and Anxiety ) እንዳሳደረብን ይታወቃል።
ይህ ደግሞ በዓዕምሮአችን ላይ የሚኖረው ተፅዕኖና የሚፈጥርብን ድብርትና አለመረጋጋት በግል፡ በቤተሰብና ማህበራዊ ህይወታችን ውስጥ አሉታዊና አግላይ ችግር ሲያስከትልብን ይታያል።
ታዲያ ይህንን ችግራችንን ከመነሻው ብንወያይበት ከባለሙያዎች ትምህርትና ምክር ብናገኝበት የግለሰብ የቤተሰብና የሕብረተሰብ ልምዳችንን ብንለዋወጥበት ጠቃሚ ትምህርት ቀስመን መረጃና መፍትሔ የምናገኝበት አይመስላችሁም?
ከመሰላችሁና ሃሳባችን ሃሳባችሁ ከሆነ፡ “ያለ ዓዕምሮ ጤና፡ ምን ህይወት አለና” በሚል መሪ ቃል የተለያዩ መንፈሳዊና ሳይንሳዊ ምሁራን የሚሳተፉበትና ከተመቻችሁ ቦታ ሆናችሁ የምትካፈሉበት የዙም (zoom) ላይ ዓውደ ጥናት ሊቀርብላችሁ ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ መሆኑን ልናበስራችሁ እንወዳለን።በዚህ ውይይት ላይ በመሳተፍ ቁም ነገር እንድታተርፉ አስቀድመን እየጋበዝን ቀኑንና ሰዓቱን በቅርብ የምናሳውቅ መሆኑን በትህትና እንገልፃለን።
እስከዚያው ቸር ሰንብቱ
The forum is expected to bring together health professionals, community members and service providers and dwell on mental health topics crucial to the Ethiopian and Eritrean communities in Toronto .
The specific details of the forum will be announced in later days . In the mean time the organizers are hoping that the community members will stay engaged in conversations around mental health issues that matter to the communities amid the COVID-19 pandemic.