የ ቶሮንቶው አሸናፊ ሶከር አካዳሚ እና የ ኪችነሩ ኢትዮ ኬ ዳብሊው የ ታዳጊዎች ማሰልጠኛዎች የወዳጅነት ግጥሚያ አደረጉ ፡፡
ከቶሮንቶ ከወላጆቻቸው ጋር ወደ ኪችነር የተጓዙት በርካታ ታዳጊዎች ከ ኪችነር አቻዎቻቸው ጋር ተጫውተዋል፡፡
የሁለቱን ከተሞች አበሻ ታዳጊዎች እና ማህበረሰቡን ለማስተዋወቅ በተደረገው ግጥሚያ የተገኙ ወላጆች የ ቡድኖቹ አሰልጣኞች እንዲሁም የኢትዮ ስታር ቡድን አመራሮች በ ዝግጅቱ መደሰታቸውን የደረሰን መረጃ ያመላክታል ፡፡
የ አሸናፊ ሶከር አካዳሚ ፕሬዝደንት እና የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ኮከብ ለኢትዮ ፊደል እንደነገረን በ ሁለቱ የካናዳ ከተሞች የሚኖሩ የ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ታዳጊዎች በ ግጥሚያው መደሰታቸውን እና ተመሳሳይ የወዳጅነት ውድድር በቶሮንቶም አስተናጋጅነት ወደፊት እንደሚካሄድ ገልጿል ፡፡
ለዝግጅቱ መሳካት ያገዙትን በሙሉ አመስግኗል
በእለቱ በ አዋቂዎች የ ቶሮንቶው ኢትዮ ስታር ቡድን እና የ ኪችነሩ አቢሲኒያ ቡድኖችም በተመሳሳይ የ ወዳጅነት ግጥሚያ አድረገዋል ፡
የ ቶሮንቶው አሸናፊ ሶከር አካዳሚ እና የ ኪችነሩ ኢትዮ ኬ ዳብሊው የ ታዳጊዎች ማሰልጠኛዎች የሜዳልያ እና ዋንጫ ሽልማቶችም ተበርክተዋል ፡፡
በቶሮንቶ እና ኪችነር ከተሞች በ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ይኖራሉ፡፡
ፎቶ ብሌን ንጉሴ እና አሸናፊ ግርማ