Following the renewed call by the prime minister of Ethiopia Abiy Ahmed, The Ethiopian Diaspora Trust Fund (EDTF) is hosting an event in Toronto . The February 16 event will take place at 958 Broadview avenue from 3 pm . In a press release sent to ethiofidel.com , the EDTF) called on Ethiopians in Toronto to come out for the event and contribute to the development of their country while learning more about the Trust fund.
የኢትዮጲያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ የካናዳ ቻፕተር ከተመሰረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ በተሮንቶና አካባቢዋ አልፎም በሌሎች ከተሞች በተለያዪ መገናኛ ዘዴዎች በመድረስ ላለፈው አንድ ወር ከፍተኛ ስራ ሲሰራ ሰንብቷል። ከተመሰረተ ገና ወር ያስቆጠረው ቻፕተሩ ከየትኛውም ቻፕሮች በቀዳሚነት ከዋናው የማስተባበሪያ ፅ/ቤት ጋር በቅርበት በመመካከር በመቋቋሙ ትክክለኛውና ህጋዊው የትረስት ፈንዱ አካል በመሆን በካናዳ የሚደረጉ የትረስት ፈንዱን አላማና ግብ የማሳወቅ፣ የመቀስቀስ፣ የማስተባበር፣ ገቢ የማሰባሰብና ማናቸውም ፈንዱን የተመለከቱ ተግባሮችን ያከናውናል፣ በባለቤትነት ይመራል። ይህንንም ለማብሰር በመጪው ፌብሯሪ 16 በ958 ብሮድ ቪው አቨኑ 3pm ባዘጋጀው ታላቅ ቻፕተሩን ይፋ የማድረግና የማስተዋወቅ ዝግጅት ላይ በመገኘት ለወገንዎ አጋርነቶን እንዲያሳዩ ጥሪውን ያቀርባል።
እንደአሚታወቀው ካናዳ የብዙህ ሺህ ኢትዮጲያዊየንና ትውልደ ኢትዮጲያዊያን መኖሪያ ናት። የኮሚዩኒቲው አባላት ላለፉት ሠላሳ ገደማ አመታት ከሀገራቸው በተለያዩ የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት በመሰደድ የካናዳ መንግስት በሚታወቅበት ስደተኞችን የመቀበል መልካም ፖሊሲና አሰራር በመጠቀም ኑሯቸውን በመግፋት ላይ ይገኛሉ።
ይህ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ አባላት የሚያስባብሩትና የሚመሩት ቻፕተሩ ካናዳ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ዘርፍ ተመዝግቦ ህጋዊ እውቅና አግኝቷል። ቻፕተሩ በዋናነት ወደ ናው የትረስት ፈንድ የኦንላይን የመለገሻ ማዕከል በኢትዮጲያ ትረስት ፈንድ ዳት ኦርግ በመግባት እንዲለግሱ የሚያበረታታ ሲሆን ይህ ስርዓት እክል ለሆነባቸው፣ አቅመ ደካሞች፣ ክሬዲት ካርድ ለሌላቸው ወይም መጠቀም ለማይሹ በቅርበት በተለያዪ ዘዴዎች ማለትም በካሽ ደረሰኝ ወይም በቻፕተሩ የቲዲ ባንክ አካውንት (በምስሉ ላይ ይመልከቱ) በቀጥታ ተቀማጭ ወይም ከግል አካውንታቸው ማዘዋወር እንዲችሉ ይንቀሰቀሳል፣ እቅድ አውጥቶ የተለያዪ መድረኮችን ያዘጋጃል፣ እንዲሁም የተለያዩ የእምነትና የማህበራዊ ዝግጅቶች ላይ በመገኘት ትምህርትና ገለፃ፣ ልገሳውን የማቀላጠፍ ስራ ይሰራል። በተጨማሪም ገንዘብ ከመሰብሰብ ባሻገር በሚታቀዱና በሚከናወኑ የልማት ዕቅዶችና ትግበራዎች ላይ የህብረየሰቡን ሃሳብና አስተያየት ያሰባስባል፣ ይህንንም ከዋናው ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ጋር በመመካከር ለውሳኔ ያቀርባል፣ የሚያጋጥሙ አዳዲስ ችግሮችንም ከህዝቡ አስተያየት በመቀበል ትረስት ፈንዱ በተቀላጠፈና በተዋጣለት መልኩ ስኬታማ በመሆን የታለመለትን ግብ እንዲመታና የጎላ ተፅዕኖውን በማሳረፍ የኢትዮጲያዊያንን ህይወት እንዲቀይር የድርሻውን ይወጣል።
እርሶም፣ እኔም፣ አንተም፣ አንቺም፣ ሁላችንም ለወገናችን ክብር ያለው ህይወት የመኖርን ዕድል ለማቀዳጀት የድርሻችንን እንወጣ። የእያንዳንዳችን በጎና ቀና ምላሽ ህይወት ይቀይራል፣ ለውጥ ያመጣል። የእርሶ፣ የእኔ፣ የአንቺ፣ የአንተ፣ የሁላችንም በቀን አንድ ዶላር ለውጥ ያመጣል፣ ህይወት ይታደጋል፣ እድል ይቀይራል። ደሞም እንችላለን!
እንዳይቀሩ! ፌብሯሪይ 16፣ ቦታ 958 ብሮድ ቪው አቨኑ ልክ 3pm። የመግቢያ ቲኬቱን ይግዙ፣ ይሳተፉ። ልብ ይበሉ ይህ የእርሶ ጉዳይ ነው። እንዳይቀሩ! ያስታውሱ 958 ብሮድ ቪው አቨኑ 3pm።
ዘሪሁን አዲሱ
የኢትዮጲያ ትረስት ፈንድ ካናዳ ቻፕተር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ