Ethiopia Bids Farewell to Vetran Politician Professor Mesfin W/Mariam

The renowned politician , human rights activist and academician Professor Mesfin Woldemariam was laid to rest today . The funeral was held at The Trinity Cathedral Church in the capital Addis Ababa .

የፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ::
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ቤተሰቦቻቸው ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና አፍቃሪዎቻቸው በተገኙበት ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል።

The prominent politician is remembered as one of the prime movers of human rights activism in Ethiopia . Amnesty international celebrated the life of Professor Mesfin with a tribute on its website . Mesfin died last week of health complications.

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ለበርካታ አስርት አመታት ሳይሰለቹ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የተሳተፉ ነበሩ ::የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ መስራች የነበሩት ፕሮፌሰር መስፍን ለሰብአዊ መብቶች መከበር ጉልህ ትግል ያደረጉ እንደነበሩ ተዘግቧል ፤፤ ኣምነስቲ ኣኢንተርናሽናልም በ ደረገጹ ላይ የህይወት ዘመን ስራቸውን የሚዘክር ፁሁፍ ኣስፍሯል

ፕሮፌሰር መስፍን ኢትዮጵያዊነትን በማቀንቀን፣ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታና ሠብዓዊ መብቶች መከበር ባደረጉት ትግልም የራሳቸውን አሻራ አሳርፈዋል።በአካዳሚክ እውቀታቸውም በድርቅና ረሃብ፣ በማህበራዊና ሌሎች መስኮች ጥናትና ምርምሮችን አድርገዋል።ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በ91 ዓመታቸው አርፈዋል።

Andienet Ayalew

Related Posts

Leave a Reply

Read also x