Former Ethiopian Prime Minister Fikreselassie Wogderes Passed Away

Ethiopia’s Former Prime Minister during the military regime passed Away. Accodrding to Ethiiopian Broadcasting Corporation, Fikreselassie passed away due to illness .

The 75 years old former official Fikreselassie was the prime minister of Ethiopia for 3 years until the down fall of the Derg millitary Regime in 1991.

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ:: ፍቅረሥላሴ ባጋጠማቸው የልብ ሕምም ምክንያት በ75 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ከ 1979 እስከ 1982 የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉ ነበሩ ። የቀብር ሥነ-ሥርዓታችው ቀን ወደፊት እንደሚገለጽ ኢቢሲ ዘግቧል።

ፍቅረሥላሴ ወግደረስ የተወለዱት ሐምሌ 7 ቀን 1937 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተለምዶ ቀጨኔ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ነው። በኢትዮጵያ አየር ኃይል ማሰልጠኛ ወጣት ካዴት ሆነው በመግባት በ1955 ዓ.ም የተመረቁ ሲሆን በአሜሪካ አገርም ስልጠና ወስደዋል። የ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት ሲፈነዳ አየር ኃይልን ወክለው የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ አባል እንደነበሩ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ፍቅረሥላሴ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ (ኢሰፓ) አደራጅ ኮሚቴ እና የደርግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ነበሩ። “እኛና አብዮቱ እና እኔና አብዮቱ” በሚል ርዕስ ሁለት መጽሐፍት ጽፈው ለአንባብያን አድርሰዋል።ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ጨምሮ 42 የደርግ አመራሮች በ1989 ዓ.ም በግድያ፣ በዘር ማጥፋት እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተከሰሱ ሲሆን በ2000 ዓ.ም የፍርድ ሂደቱ ሲጠናቀቅ በተከሰሱበት ወንጀል የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ነበር። በ2003 ዓ.ም የፍቅረሥላሴን እና ሌሎች 23 የደርግ አመራሮች የሞት ቅጣት ተነስቶ በ2004 ዓ.ም ከእስር እንዲፈቱ መደረጉ አይዘነጋም።የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ በተለይም የኢትዮጵያ ታሪክ ለትውልድ ተሰንዶ እንዲቀመጥ የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ እንደሚታወቁ ይነገራል።ፍቅረሥላሴ ወግደረስ የሁለት ሴት እና የአንድ ወንድ ልጅ አባት እንደ ነበሩ።

The former prime minister who was born in the capital Addis was an airforce officer before be ascended to become the prime minister of the country .

Fikresellasie was one of the military regime officials who were sentenced to death for murder, human rights violations and genocide charges after a trial that lasts between 1996 and 2008. The government of Ethiopia commuted his death sentence and released him from prison after serving being in prison for 20 years.

Fikreselassie wrote two books around the events during the Derg regime .

Source EBC

Andienet Ayalew

Related Posts

Leave a Reply

Read also x