Ethiopian Canadians raised More than 250,000 Canadian dollars for Internally displaced people in Ethiopia

Ethiopian Canadians raised More than 250,000 Canadian dollars for Internally displaced people in Ethiopia.

At a fundraising event organized by The Ethio-Canadian Network for Social Assistance (ECNAS) Toronto Chapter, more than $250,000 CAD has been raised for the benefit of displaced people in Ethiopia’s Amhara and Afar regions. According to statement by ECNAS, The proceedings will benefit those displaced by the attacks from the terrorist- designated rebel group TPLF.

The money was raised through various aivities at the event .

In a sold out fundraising event, an estimated 1,500 Ethiopians from Toronto and other cities gathered at the Lithuanian hall chanting patriotic songs .

Canadian journalist Jeff Pearce and Professor  Ann Fitz Gerald were also recognized for their contribution in standing with Ethiopians during the time of adversaries . They were praised for their efforts in telling the facts to the international community as opposed to the biased coverage by the international media .

Both urged for the #nomore movement to continue with the same passion for Ethiopia and the rest of Africa should decide their own fate. As Jeff Pearce characterized it , the #nomore movement is a “re- birth of Pan Africanism.”

Ethiopian artists residing in Toronto also performed at the event .   

ECNAS told Ethiopian News Agency ( ENA) that it has planned to raise 200,000 Canadian dollars and raised more than 250,000 Canadian dollars during the program. Please read the statement below from ECNAS Toronto Chapter board.

በቶሮንቶ ኢትዮጵያዊነት በነገሰበት የእራት ምሽት ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ከ 200 ሺህ የካናዳ ዶላር በላይ ተሰበሰበ በቶሮንቶና ሃሚልተን የሚገኙ የኢትዮ-ካናዳውያን ኔትዎርክ ለማህበራዊ ድጋፍ -(ECNAS-Toronto Chapter) አባላት እና ደጋፊዎች ቅዳሜ December 4, 2021 ባደረጉት የ እራት ምሽት 200 ሺህ የካናዳ ዶላር (ወይም ከ 8 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ) ተገኝቷል። ይህ ማለት ኢክናስ ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ያሰባሰበውን እና ወደ ኢትዮጵያ የላከውን የቁሳቁስ እና የገንዘብ ዕርዳታ መጠን ከ 160 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ ያደርሰዋል። በምሽቱ የተሰበሰበው ዕርዳታ በአማራ እና በአፋር ክልሎች ለተፈናቀሉ እና በ ህወሃት ወራሪ ሃይሎች ከፍተኛ በደል እና ሥቃይ ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ድጋፍ የሚውል ነው።

በኢክናስ አሠራር መሠረት ከተዋጣው ገንዘብ ምንም አስተዳደራዊ ወጪ ሳይቀነስ በቀጥታ ለተረጂዎች የሚደርስ ይሆናል።ዝግጅቱ በቶሮንቶ ታሪክ ካሁን በፊት ታይቶ የማይታወቅ፤ ህዝቡ ንቅል ብሎ በመውጣቱ ከ3 አዳራሾች ተርፎ ረጅም ሠልፍ የታየበት እና ብዙ ህዝብ መግባት ያልቻለበት ነበር። አዘጋጆቹ የቶሮንቶ ኢክናስ አመራሮች በጊዜው ባለው የኮቪድ ጥንቃቄ እና በክረምቱ መግባት ምክንያት በተሸጠው የትኬት ልክ መጠን ህዝብ ይመጣል ብለው ባይገምቱም 3 አዳራሾችን በመያዝ ያደረጉት ጥንቃቄ ሊፈጠር የሚችለውን ችግር በከፍተኛ ደረጃ አቃሎታል። መግባት ያልቻሉ ወይም ረጅም ሠልፍ ይዘው የጠበቁ የቶሮንቶ እና አካባቢው ነዋሪዎች “የመጣነው ወገናችንን ለመርዳት ስለሆነ መግባት ባንችል እንኳን የትኬቱን ዋጋ ገንዘብ እንክፈላችሁ እና እንመለስ” በማለት ፍፁም ኢትዮጵያዊ የሆነ ፍቅር እና ትዕግሥት ስላሳዩን ምሥጋናችን እጅግ ከፍተኛ ነው። ይሁን እንጂ የቶሮንቶ ኢክናስ የቦርድ አባላት በምሽቱ መጉላላት የደረሰበት አንድም ታዳሚ እንኳን ቢኖር ይቅርታ ይጠይቃሉ።

ሀገራችንና ህዝባችንን ከተጋረጠባቸው ሰፊ አሰቃቂና ውስብስብ ችግሮች ለማውጣት ቀጣይ እንቅስቃሴዎችን ስለምናደርግ የሁልጊዜም ትብብራችሁ እንደማይለየንም ሙሉ ተሥፋ አለን።በዝግጅቱ ላይ ታዋቂው የካናዳ ጋዜጠኛና የታሪክ ፀሃፊ ጄፍ ፒርስ እንዲሁም ፕሮፌሰር አን ፊትዝጄራልድ ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅዖ የተዘጋጀላቸውን ሽልማት በ ዕለቱ ሌላው የክብር እንግዳ ከነበሩት አምባሳዶር ካዴፎ መሃመድ ሃንፋሬ የተቀበሉ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ ለጨረታ የቀረበው የአፋር ጎራዴ 20 ሺህ የካናዳ ዶላር አስገኝቷል። ይህ ዝግጅት እንዲሳካ ምግብ እና መጠጥ በነፃ በመስጠት ለተባበሩን ሬስቶራንቶች እና ሌሎች የንግድ ተቋማት እና ግለሰቦች፤ ዝግጅቱን ስፖንሰር በማድረግ ለተባበሩን ቢዝነሶች፤ ዝግጅቱን ላደመቁልን ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች፤ዝግጅቱን በመራው ግብረ-ሃይል ውስጥ በተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ ለተሳተፉ አባሎቻችን እና በጎ-ፈቃደኞች፤ ትኬት በመግዛት እና የተለያዩ ሥጦታዎችን በመስጠት ለተባበሩን የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ኮሚዩኒቲ አባላት በሙሉ ምሥጋናችንን እናቀርባለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

የኢክናስ ቶሮንቶ ቻፕተር ቦርድ

Photo from Teklemichael Abebe ( FB)

Yohannes Ayalew

Related Posts

Leave a Reply

Read also x