Ethiopian Legesse Moges Received International Award by British Military

Ethiopian army Cadet Legesse received the International Medal at Royal Military Academy Sandhurst in the UK. The award is given for high performance in education, training and physical fitness fields displayed during the training period.

Legesse received his medal from Princess Anne of England . Reviving this award made Legesse very proud ” This award at this moment is great joy for me and my country . He attributed hard work and focus to his success.

“I was shaking when they called Ethiopia’s name at the award ceremony” says Cadet Legesse while promising to serve his country , Ethiopia in any capacity.

ኢትዮጵያዊው ለገሰ ሞገስ በወታደራዊ መኮንንነት በአለም ዝነኛ በሆነው የሮያል ሳንድረስት የጦር አካዳሚ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል።

በእንግልዝ UK ዝነኛው የሮያል ሳንድረስት የጦር አካዳሚ ባለፈው አመት ከ38 ሀገሮች ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችን መልምሎ በሰጠው ወታደራዊ ስልጠና ኢትዮጵያዊው ለገሰ ሞገስ ከሁሉም ሀገሮች ሰልጣኞች በሁሉም ወታደራዊ ጥበብ መስኮች በጦር መኮንንነት በጦር ንድፈ ሀሳብ እና የጦር ተግባራዊ ሳይንስን በተመለከተ ባሳየው ጥበብና እውቀት ብልጫ በማሳየቱ የወርቅ ሜዳሊያ እንደተሸለመ በምረቃው ስነስርአት ላይ ተገልጿል።

ለገሰ ሞገስ ዘመኑ የደረሰበትን ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብበተሟላ መልኩ በመፈጸሙ የጦር አካዳሚው የሚሰጠውን ከፍተኛ ሜዳሊያ ከመላው ሀገሮች የተወከሉ ወታደራዊ የጦር መኮንኖች የእንግሊዝ ልኡላዊያን ቤተሰቦች የተለያዩ ሀገሮች አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች እንዲሁም የሮያል ሳንድረስት የጦር አካዳሚ አመራሮች በተገኙበት የእንግሊዝ ልእልት አን እጅ የወርቅ ሜዳሊያውን ተቀብሏል።

በምረቃው ስነስርአት ላይ የተገኙት በለንደን የኢፌዲሪ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ እንደተናገሩት ይህ ወጣት የጦር መኮንን ዘመኑ ያፈራውን ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ በብቃት አጠናቆ የላቀ ውጤት በማምጣቱ እና የሀገሩን ስም በምረቃው ስነስርአት ላይ በክብር እንዲነሳ ማድረጉ ለሁሉም ኩራት ነው ብለዋል ።አክለውም ኢትዮጵያዊያን በየተሰማራንበት በትጋት ከሰራን ለማሸነፍ ምንም የሚያግደን ምክንያት እንደሌለ የዛሬው የክብር ተመራቂ ለገሰ ሞገስ አርአያ በመሆን ያስመሰከረ ነው ብለዋል፡፡ከበርካታ አመታት በኃላ በሮያል ሳንድረስት የጦር አካዳሚ የወታደራዊ መኮንንነት ትምህርት እድል ያገኘው ለገሰ ሞገስ በበኩሉ ወገኖቼ የሀገራቸውን አንድነት ለማስከበር በዱር በገደሉ እየተዋደቁ እና ህይወታቸውን ለሀገራቸው ክብር እየሰጡ ባሉበት ወቅት ልቤ እነርሱ ጋር ሆኖ ለዚህ ክብር መብቃቴ ሽልማቱ የእነርሱም ጭምር ነው በማለት ተናግሯል፡፡

Watch the video from this link

https://www.facebook.com/100005417983049/videos/3059062764336740/

From Ethiopian Ministry Of Foreign Affairs

Photo – Ethiopian Embassy London

Yohannes Ayalew

Related Posts

Leave a Reply

Read also x