Ethiopian Artist Zenebu Gessesse Passed Away

ለ 35 አመታት በኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ውስጥ የራሷን አሻራ ያኖረችው አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ በዛሬው ዕለት አርፋለች።

አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ በርካታ ፊልሞችን እና የቴሌቭዥን ድራማዎችን ከመስራት ባለፈ በውዝዋዜ ሙያ ሀገሯን ስታገለግል ነበር ።


አርቲስቷ ካላት የኪነ ጥበብ ችሎታ ባለፈ በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ በማድረግም ትታዉቃለች ።

አርቲስቷ ባደረባት የጡት ካንሰር ህመም በሕክምና ስትረዳ ቆይታ ዛሬ ቡልቡላ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች።

የአርቲስት ዘነቡ ገሠሠ የቀብር ስነ ስርአት በነገው ዕለት (17/08/2014 ዓ.ም ) በቡልቡላ መድሀኒ አለም ቤተክርስቲያን ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ላይ እንደሚፈፀም አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ከራስ ቲያትር የሙያ ባልደረቦቿ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ የሁለት ሴቶች እና የሁለት ወንዶች እናት ነበረች። ሁለት የልጅ ልጆችን አይታለች።

ኢትዮፊደልለአርቲስቷ ቤተሰቦች፣ አድናቂዎች እና ወዳጆች ሁሉ መጽናናትን ይመኛል።

Source Addis Media Network

Yohannes Ayalew

Related Posts

Leave a Reply

Read also x