Ashenafi Soccer Academy and Kitchener Ethio- KW Played Friendly Match

የ ቶሮንቶው አሸናፊ ሶከር አካዳሚ እና የ ኪችነሩ ኢትዮ ኬ ዳብሊው የ ታዳጊዎች ማሰልጠኛዎች የወዳጅነት ግጥሚያ አደረጉ ፡፡

ከቶሮንቶ ከወላጆቻቸው ጋር ወደ ኪችነር የተጓዙት በርካታ ታዳጊዎች ከ ኪችነር አቻዎቻቸው ጋር ተጫውተዋል፡፡

የሁለቱን ከተሞች አበሻ ታዳጊዎች እና ማህበረሰቡን ለማስተዋወቅ በተደረገው ግጥሚያ የተገኙ ወላጆች የ ቡድኖቹ አሰልጣኞች እንዲሁም የኢትዮ ስታር ቡድን አመራሮች በ ዝግጅቱ መደሰታቸውን የደረሰን መረጃ ያመላክታል ፡፡

የ አሸናፊ ሶከር አካዳሚ ፕሬዝደንት እና የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ኮከብ ለኢትዮ ፊደል እንደነገረን በ ሁለቱ የካናዳ ከተሞች የሚኖሩ የ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ታዳጊዎች በ ግጥሚያው መደሰታቸውን እና ተመሳሳይ የወዳጅነት ውድድር በቶሮንቶም አስተናጋጅነት ወደፊት  እንደሚካሄድ ገልጿል ፡፡

ለዝግጅቱ መሳካት ያገዙትን በሙሉ አመስግኗል

በእለቱ በ አዋቂዎች  የ ቶሮንቶው ኢትዮ ስታር ቡድን እና የ ኪችነሩ አቢሲኒያ ቡድኖችም በተመሳሳይ የ ወዳጅነት ግጥሚያ አድረገዋል ፡

የ ቶሮንቶው አሸናፊ ሶከር አካዳሚ እና የ ኪችነሩ ኢትዮ ኬ ዳብሊው የ ታዳጊዎች ማሰልጠኛዎች የሜዳልያ እና ዋንጫ ሽልማቶችም ተበርክተዋል ፡፡

በቶሮንቶ እና ኪችነር ከተሞች በ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ይኖራሉ፡፡

ፎቶ ብሌን ንጉሴ እና አሸናፊ ግርማ  

Yohannes Ayalew

Related Posts

Leave a Reply

Read also x