Renowned Ethiopian Radio and TV Icon Asfaw Meshesha Passes Away, Leaving a Lasting Legacy in Entertainment

Renowned Ethiopian Radio and TV Icon Asfaw Meshesha Passes Away. Ethiopians across the globe are mourning his death reflecting on his legacy .

ታዋቂው የሬድዮ እና ቲቪ ፕሮግራም አዘጋጅ እና አቅራቢ አስፋው መሸሻ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

ኢትዮጵያ በአገሪቷ የመዝናኛ ኢንዳስትሪ ውስጥ ትልቅ ሚና የተጫወተውን አስፋው መሸሻን በማጣቷ ሃዘን ላይ ነች። ታዋቂው የሬዲዮና የቲቪ ፕሮግራሞች አዘጋጅ እና አቅራቢ አስፋው መሸሻ በ1990ዎቹ በኤፍ ኤም 97.1 ላይ “አይሪ” የተሰኘውን የሬዲዮ ፕሮግራም በ ማቅረብ የ መዝናኛ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ፕሮግራም ፋና ወጊዎች ውስጥ ዋነኛው ነበር ፡፡

ኢትዮጵያ አንድ የኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ብቻ በነበራት ጊዜ የአስፋው የራዲዮ ፕሮግራም እና ልዩ የሙዚቃ ምርጫ  በሀገሪቱ የአየር ሞገድ ላይ የማይሽር አሻራ ጥሏል።  የ አስፋው ሙያዊ አበርክቶ ወደ ቴሌቭዥን ከገባ ወዲህም  በኢቢኤስ ቲቪ “ኑሮ በ አሜሪካ” የተሰኘ የቃለ ምልልስ ፕሮግራም አዘጋጅቶ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ህይወት ይዳስስ ነበር ፡፡

አስፋው መሸሻ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በኢቢኤስ ቴሌቭዥን የመዝናኛ ሾው ላይ በ ተመልካቾች እጅግ ተወዳጅነትን አትርፎ ቆይቷል ። በፕሮግራሞቹ ላይ ከሚቀርቡት እንግዶች ጋር ጥልቅ ስሜታዊ ተግባቦት የነበረው አስፋው ከሚደንሱት ደንሶ ከሚያዝኑም ጋር አልቅሶ ለሰው ልጆች ያለውን ሃዘኔታ ያሳይ እንደነበር የሙያ ባልደረቦቹ በማህበራዊ ድረገጾቻቸው ባሰፈሩት የሃዘን መግለጫ አውሰተዋል፡፡

አስፋው ባጋጠመው ህመም በ አሜሪካ ህክምና ሲያደርግ ቆይቶ ትላንት ነው ያረፈው ፡፡ የህልፈቱ ዜና በአለም ዙሪያ ባሉ አድናቂዎች ዘንድ ሃዘን እና ድንጋጤን ፈጥሯል ፣“ በ ቤታችን እንደሚኖር አንድ የቤተሰብ አባል ያህል ነው የአስፋው ሞት ውስጤ የገባው “ ብላለች የ ቶሮንቶ ነዋሪ ትእግስት ለ ኢትዮፊደል አዘጋጅ እንደተናገረችው ፡፡

ለ አስፋው ያለውን አክብሮት ለመግለጽ ኢቢኤስ ቲቪ የ መደበኛ ፕሮግራሞቹን ለጊዜው አቋርጧል።

አስፋው መሸሻ ለሚዲያ ካበረከተው አስተዋፅዖ ባሻገር በበጎ አድራጎት ስራ ውስጥም ይሳተፍ እንደነበር ተነግሯል ። ከመዝናኛ ባሻገር በጎ ስራ ላይ ያለውን ቁርጠኝነት በማሳየት በአንድ ወቅት ከአባቱ የተበረከተለትን መኪና  ለበጎ አድራጎት ተግባር  በልግስና አበርክቶ እንደነበር ተጠቅሷል።

Renowned Ethiopian Radio and TV Icon Asfaw Meshesha Passes Away, Leaving a Lasting Legacy in Entertainment

In a somber turn of events, Ethiopia mourns the loss of Asfaw Meshesha, a trailblazing figure in our nation’s entertainment industry. Asfaw, a prominent radio and TV host and producer, gained widespread recognition as a pioneer during the early 2000s when he co-produced the “Irie” music radio show on FM 97.1.

During a time when Ethiopia had just one FM radio station, Asfaw’s radio program and music selection stood out. His influence extended to television, where he hosted an interview show on EBS TV, shining a spotlight on the lives of Ethiopians in North America.

Until recently, Asfaw Meshesha continued to be popular among  audiences as a co-host on an entertainment show on EBS TV. Known for his empathetic on-air persona, Asfaw emotionally immersed himself in the diverse stories of people from all walks of life. Whether dancing or shedding tears alongside his guests, he connected with viewers on a deeply emotional level.

Asfaw was receiving medical treatment in the United States. The news of his passing has sent shockwaves among fans worldwide, prompting an outpouring of condolences on social media.

In a gesture of respect, EBS TV has temporarily discontinued its regular programming to honor Asfaw.

Beyond his contributions to the media landscape, Asfaw Meshesha was also recognized for his contribution to philanthropy. He generously donated a car, a gift from his father, to a charitable cause.

Yohannes Ayalew

Related Posts

Leave a Reply

Read also x