A Dedicated civil servant and a caring family man
Tamrat Gebeyehu , an Ethiopian Canadian law professional and a well-known community activist in Toronto passed away this week . Tamrat was working for the Federal ministry of Justice in Canada as a legal counsel. During his tenure, he received special award of merit in the department. He also served as a law professor at Humber College where he inspired and mentored young law professionals. After completing his law school at University of Toronto in 2001, he was called to the law Bar in Ontario.
በካናዳ ቶሮንቶ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ የህግ ባለሙያ እና የማህበረሰብ ኣገልጋይ እንዲሁም የውጫሌ 17 ቲያትር ደራሲ የነበሩት ኣቶ ታምራት ገበየሁ ኣረፉ
የ ቀብር ስነስርአታቸውም ቶሮንቶ ውስጥ ተፈፅሟል
In an emotional testimony at his funeral in Toronto’s St Mary Ethiopian Orthodox Church, Tamrat’s coworkers remembered him as a kind, intelligent, and dedicated colleague and a family man.
The love of Art , the Love of Ethiopia
Tamrat was all about Art. Prior to coming to Canada, he graduated as a distinction student in the department of theatrical arts. He wrote and directed a famous play entitled Wuchale 17 which was staged at the National Theater in Ethiopia. Tamrat also received his postgraduate degree at the University of Edmonton in Canada.
In an even more passionate speech at the funeral, members of the Haddis Nigat Arts Forum (which he founded), Bayu Kidane and Petros Dejene chronicled how Tamrat shaped the movement to the reservation of Ethiopian literature and tradition. They looked back at Tamerat’s legacy of working hard to bring Ethiopians together through his artistic works and community involvement. Tamrat directed and played in several plays in Toronto .Between 2009 and 2012, Tamrat, also co-hosted Ethiopian Community Radio in Toronto.
Tamerat’s community activism spanned from being a board member at the P2P Canada, Ethiopian Association and Bikilla Award to being artistic Director of Haddis Nigat Arts Forum.
The late Tamrat who passed away on May 16 due to serious illness is survived by his wife and two daughters.
በካናዳ ቶሮንቶ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ የህግ ባለሙያ እና የማህበረሰብ ኣገልጋይ ኣቶ ታምራት ገበየሁ ኣረፉ
የ ቀብር ስነስርአታቸውም ቶሮንቶ ውስጥ ተፈፅሟል
አቶ ታምራት ገበየሁ ከእናታቸው ከወይዘሮ አጸደ ወ/ሰማያት እና ከአባታቸው ከአቶ ገበየሁ ተገኝ ሰኔ 7 ቀን 1955 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ:: በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቲያትር ጥበባት ትምህርታቸውን ተከታትለው እጅግ በላቀ ውጤት የዲፓርትመንታቸውን ከፍተኛ ልዩ ማዕረግ አግኝተው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል።
አቶ ታምራት ውጫሌ 17 የተባለውን በሕዝብ ዘንድ አድናቆትን ያተረፈውን ቲያትር በመድረስና በማዘጋጀት በብሔራዊ ቲያትር ለመድረክ አብቅተዋል።
ወደ ቀድሞው የሶቪየት ሕብረት ተልከው የሥነ ጥበብ ትምህርታቸውን በ1987 ዓ/ም ወደ ካናዳ መጥተውም በኤድመንተን ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ሠርተዋል።
በቶሮንቶ ዮርክ ዩኒቨርሲቲ ለተጨማሪ አራት ዓመታት የሕግ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ በኋላ ከ2001 ዓ/ም ጀምሮ የሕግ ጥብቅና ፈቃዳቸውን አግኝተዋል።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በካናዳ የፌዴራሉ መንግሥት የፍትህ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ውስጥ የሠሩ ሲሆን ከዚያም በኋላ በዚሁ መሥሪያ ቤት በፍትህ ሚኒስቴር ሕግ አማካሪነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
አቶ ታምራት ገበየሁ ተተኪውን ትውልድ ለመገንባት ካላቸው ጽኑ ዕምነት አኳያ በሀምበር ኮሌጅ በርካታ የሕግ ተማሪዎችን አስተምረዋል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያውያን ማህበር በቶሮንቶ በቦርድ አባልነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ በመሆን እና ቶሮንቶ በሚገኘው ሀዲስ ንጋት የኪነ ጥበብ መድረክ ከምሥረታ ጀምሮ በቦርድ አባልነትና በአርቲስቲክ ዳይሬክተርነት በመሳተፍ የተለያዩ ድራማዎችንና ሥነጽሁፎችን በመድረስና በማቅረብ በኪነጥበብ ዘርፍ ድርሻቸውን አበርክተዋል። የቢቂላ ድርጅት መሥራች አባል ና ጸሐፊም ነበሩ፤፤ ከዚህም ሌላ በ በኢትዮጵያውያን ማህበር በቶሮንቶ የ ሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ኣገልግለዋል ፥፥
በ ቶሮንቶ ቅድስት ማሪያም የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ካቴድራል በተካሄደው ፍትሀት ላይ የ ኣቶ ታምራት ወዳጅ ዘመዶች እና ቤተሰቦች ስለ ኣቶታምራት ንግግር ኣድርገዋል
ኣቶ ታምራት ቅን ሌሎች እንዲያድጉ የሚረዱ ቤተሰባቸውን ወዳጅ እንደነበሩ የ ስራ ባልደረቦቻቸው መስክረዋል
ሰሜት የተቀላቀለበት ንግግር ያደረጉት የ ሀዲስ ንጋት የ ኪነጥበብ መድረክ ኣባላት ኣቶ ባዩ ኪዳኔ እና ኣቶ ጴጥሮስ ደጀኔ ኣቶታምራት ለኢትዮጵያዊ ባህል እና ታሪክ መጠበቅ ላደረጉት ኣስተዋፃኦ እና ለጠንካራ ስብእና ተምሳሌትነታቸው ዘክረዋቸዋል፥፥
ኣቶ ተሰማ እና ዶክተር ህሊናም እንዲሁ የ ኣቶ ታምራትን መልካምነት እና የ ቤተሰቦቻቸውን ጥንካሬ ኣውስተዋል ፤፤
በ ኣሜረካ የሚገኘው እና በ ታዋቂዋ ኣርቲስት ኣለም ፀሀይ ወዳጆ የሚመራው ጣይቱ የ ባህል ማእከልም ለ ኣቶ ታምራት ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል
የ ኢትዮ ፊደል ኣባላትም ለ ኣቶ ታምራት ቤተሰቦች እና ወዳጆች ፈጣሪ ያጽናናችሁ እንላለለን