An Ethiopian Physician in Poland is organizing a volunteer medical team to travel to Ethiopia.
ኢትዮጵያዊው ዶክተር ብዙአየሁ መንገሻ 13 የሚሆኑ ፖላንዳውያን ስፔሻሊስት ሀኪሞች እንዲሁም ነርሶችን አስተባብረው ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ነው።
Dr. Bezuayehu Mengesha is travelling with a team of 13 Polish medical professionals to Ethiopia .Tikvak reported that the specialist doctors and nurses will be assisting patients. The team of seasoned medical professionals is also travelling with medical equipment worth 1.5 million Ethiopian Birr.
በዶክተር ብዙአየሁ የሚመራው ቡድን ያሰባሰበውን ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የህክምና እቃዎችንና መድሀኒቶችንም ለወገኖቻችን ይዞ እየመጣ ይገኛል።
ከፖላንድ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ የጀመሩት በጎ ፈቃደኞች የተጎዱ ወገኖቻችንን በሕክምና የሚረዱ ሲሆን ዘመናዊ የህክምና መሳርያዎችን የያዙ እና የብዙ አመት ልምድ ያላቸው ስፔሻሊስቶች ናቸው።
ለ10 ያህል ቀናት በኢትዮጵያ የሚቆየው ቡድኑ ከፊታችን ማክሰኞ ጀምሮ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህን መልዕክት ከፖላንድ ሀገር የላከልን የቤተሰባችን አባል ፥ዶ/ር ብዙአየሁ በጭንቅ ጊዜ ለወገኑ የቆመ ከወሬ ይልቅ በተግባር ሰርቶ ያሳየ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነው ለዚህም እናመሰግነዋለን ብሏል።
(አቤነዘር ተስፋዬ – ከፖላንድ)
Source :Tikvah Ethiopia