Ethiopia’s social media award, Tana Award, recognized social media influencers in Ethiopia. Fifteen individuals and social media outlets were awarded at a ceremony organized by Zemera Multi media and solomonic Entertainment in the city of Bahirdar.
በዘመራ መልቲ ሚዲያና ፕሮሞሽን እና ሰሎሞኒክ ኢንተርቴይመንት “ማኅበራዊ ሚዲያ ለሚዛናዊ መረጃ፣ ለበጎ ተግባርና ለኢትዮጵያዊነት ” በሚል መሪ ሐሳብ በባህርዳር ከተማ በብሉ ናይል ሪዞርት ሆቴል ሲከናወን የነበረው የ2010 ዓ.ም ሁለተኛው ጣና ሽልማት አሸናፊዎች ተለይተዋል፡፡
በዚህም መሠረት
1- በፈጣን ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ በስነጹሁፍ ዘርፍ
# ጌጡ ተመስገን(ለሁለተኛ ጊዜ)
2- በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ
# ጌትነት ተመስገን
3- በስፖርት መረጃ ዘርፍ
# ሶከር ስፖርት
4- በሥነ-ጥበባዊ ምስሎች እና ትርክቶች ዘርፍ
# እያዩ ገነት
5- በፎቶ ግራፍ ዘርፍ
# ኢትዮጲክስ
6- በጤና መረጃ ዘርፍ
# ዶክተር አለ
7- በሥነ-ፅሁፍ ዘርፍ
# ዲያቆን ዲንኤል ክብረት
8- በታሪክ ዘርፍ
# እዮብ ዘለቀ
9- በንግድና ቢዝነስ ዘርፍ
# ሄሎ መርካቶ
10- በትምህርትና ማህበረሰብ ግልጋሎት ዘርፍ
# ብክ ፎር ኦል
11- በጥናትና ምርምር ዘርፍ
# ባህርዳር ዩኒቨርስቲ
12- በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ
#ሳይ ቴክ
13- በበጎ አድራጎትና አካባቢ ልማት ዘርፍ
# አቦጊዳ
14 በፈጣን ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ በዮቲዮብ ዘርፍ
# የኛ ቲዮብ
15- ልዩ ተሸላሚ
# ቢኒያም ነገሱ
የድሬ ቱዮብ መስራች እና ባለቤት