የ ቶሮንቶው አሸናፊ ሶከር አካዳሚ እና የ ኪችነሩ ኢትዮ ኬ ዳብሊው የ ታዳጊዎች
ማሰልጠኛዎች የወዳጅነትየመልስ ግጥሚያ አደረጉ፡:
ኦገስት 13 ፣ 2022 በ ቶሮንቶው ሞናርክ ፓርክ ስቴዲየም በ አሸናፊ ሶከር አካዳሚ አስተናጋጅነት የሁለቱ ከተሞች ታዳጊዎች ግጥሚያ አድርገዋል ፡፡
የታዳጊዎቹ ወላጆች የቶሮንቶ ነዋሪች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ታዳጊዎቹን አበረታተዋል::
በ ውድድሩ የተካፈሉት ታዳጊዎች የተዘጋጀላቸውን ሚዳልያዎች ከ ክብር እንግዶች ወስደዋል ፡፡
የ አጼ ሃይለስላሴ የልጅ ልጅ የሆኑት ልኡል በእደማርያም መኮንን፣ የ ቶሮንቶ ነዋሪ እና በ አገራችን ስፖርት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸውአቶ ታምሩ ተስፋዬ ፡ ታዋቂዎቹ የ ኢቲቪ የ ስፖርት ጋዜጠኞች ዮናስ ተሾመ፡ እና ዮናስ ሃይለመስቀል፣ እንዲሁም አቶዳዊት ተስፋዮ ዶ/ር ሙሉ ገለቱ እና ጋዜጠኛ ኢልያስ አወቀ ከ አሸናፊ ሶከር አካዳሚ ፕሬዝዳንት አሸናፊ ግርማ ጋር በመሆን ሜዳልያዎችን አበርክተዋል ፡፡
Photo by Etsubdink Lealem