Ashenafi Girma Soccer Academy and Kitchener’s Ethio KW Friendly Match

የ ቶሮንቶው አሸናፊ ሶከር አካዳሚ እና የ ኪችነሩ ኢትዮ ኬ ዳብሊው የ ታዳጊዎች

ማሰልጠኛዎች የወዳጅነትየመልስ ግጥሚያ አደረጉ፡:

ኦገስት 13 ፣ 2022 በ ቶሮንቶው ሞናርክ ፓርክ ስቴዲየም በ አሸናፊ ሶከር አካዳሚ አስተናጋጅነት የሁለቱ ከተሞች ታዳጊዎች ግጥሚያ አድርገዋል ፡፡

 የታዳጊዎቹ ወላጆች የቶሮንቶ ነዋሪች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ታዳጊዎቹን አበረታተዋል::

በ ውድድሩ የተካፈሉት ታዳጊዎች የተዘጋጀላቸውን ሚዳልያዎች ከ ክብር እንግዶች ወስደዋል ፡፡

የ አጼ ሃይለስላሴ የልጅ ልጅ የሆኑት ልኡል በእደማርያም መኮንን፣ የ ቶሮንቶ ነዋሪ እና በ አገራችን ስፖርት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸውአቶ ታምሩ ተስፋዬ ፡ ታዋቂዎቹ የ ኢቲቪ የ ስፖርት ጋዜጠኞች ዮናስ ተሾመ፡ እና ዮናስ ሃይለመስቀል፣ እንዲሁም አቶዳዊት ተስፋዮ ዶ/ር ሙሉ ገለቱ እና ጋዜጠኛ ኢልያስ አወቀ ከ አሸናፊ ሶከር አካዳሚ ፕሬዝዳንት አሸናፊ ግርማ ጋር በመሆን ሜዳልያዎችን አበርክተዋል ፡፡

Photo by Etsubdink Lealem

Yohannes Ayalew

Related Posts

Leave a Reply

Read also x