Ethiopia’s First Sports Journalist Fikru Kidane passed away

The prominent Ethiopian sports leader, journalist and author Fikru Kidane passed away at the age of 78.

The former member of the International Olympic comitee and a famous sportsman died of illness in Paris France .

The Addis based Leuge sports , reported that Fikru Kidane was the first person who did a live sports commentary on a radio in Ethiopia.

በስፖርት ጋዜጠኝነት ፣ አመራርነት እና ደራሲነት የሚታወቁት አንጋፋው የስፖርት ሰው አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አቶ ፍቅሩ በኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኝነት ታሪክ ፈር ቀዳጅ ከሚባሉ ግለሰቦች አንዱ እንደነበሩና የእግር ኳስ ጨዋታን በቀጥታ በሬዲዮ በማስተላለፍ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ እንደነበሩ የሚነገርላቸው ሲሆን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በተለያዩ ቋንቋዎች የስፖርት ዘገባዎችን በማቅረብ ፣ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፣ በካፍ እና በኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራርነት ፣ በጋዜጠኞች ማህበር መስራችነት እና አመራርነትም ከፍተኛ ግልጋሎት ሰጥተዋል። ” የፒያሳ ልጅ ” በተሰኘው መፅሀፋቸው እና ሌሎች መፅሐፍቶችም ከፍተኛ እውቅና ያገኙ ምርጥ ደራሲ ነበሩ።

አንጋፋው የስፖርት ሰው አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ በ ተለያዩ ጊዜያት ወደ ቶሮንቶ ካናዳ በመምጣት በስፓርታዊ ክንዋኔዎች ላይ ንግግሮች አድርገዋል ።

Yohannes Ayalew

Related Posts

Leave a Reply

Read also x